የሀገር ውስጥ ዜና

ጠ/ሚ ዐቢይ (ዶ/ር) የፈረንጆቹን የገና በዓል ለሚያከብሩ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ

By ዮሐንስ ደርበው

December 25, 2023

አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 15፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የፈረንጆቹን የገና በዓል ለሚያከብሩ የእንኳን አደረሳቹ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት፥ ለመላው የኢትዮጵያ ወዳጆች፣ ለዳያስፖራው ማኅበረሰብ እና ለዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ መልካም የገና በዓል እንዲሆንላችሁ እመኛለሁ ብለዋል።

የገና በዓል የኢየሱስ ክርስቶስ መወለድን አስመልክቶ በተለያዩ የዓለም ክፍሎች በዛሬው ዕለት በሐይማኖታዊ እና ባሕላዊ ሥነ-ሥርዓቶች እየተከበረ ነው፡፡

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/ ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!