አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 15፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ምክትል ገዥ የተመራ ልዑክ ከቻይና ማዕከላዊ ባንክ ጋር በቀጣይ በሚከናወኑ የቴክኒክ ትብብሮች ላይ ፍሬያማ ውይይት አድርጓል፡፡
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ምክትል ገዥን ጨምሮ ከፍተኛ አማካሪዎችን እና ዳይሬክተሮችን ያካተተ ልዑክ በቻይና ቤጂንግ፣ ሻንጋይ እና ሼንዘን ጉብኝት አድርጓል፡፡
ጉብኝቱም ቻይና በፋይናንሱ ዘርፍ ራሷን የቻለችበትን መንገድ፣ ከውጭ ባንኮች ጋር ያለውን ውኅደት እና የካፒታል ገበያ እድገቷ ላይ ግንዛቤ ለማግኘት ያለመ መሆኑ ተገልጿል።
ይህም ኢትዮጵያ በጉዳዩ ላይ ለምታከናውነው ሥራ ዐቅም እንደሚሆን ነው የተገለጸው፡፡