የሀገር ውስጥ ዜና

በሀገራዊ ምክክሩ ትኩረት የሚሹ ጉዳዮችን በመለየት በጊዜ እንዲጠናቀቅ ርብርብ ሊደርግ ይገባል – አፈ ጉባዔ ታገሰ ጫፎ

By Shambel Mihret

December 26, 2023

አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 16፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በሀገራዊ ምክክሩ ትኩረት የሚሹ ዋና ዋና ጉዳዮችን በመለየት በተፈለገው ጊዜ እንዲጠናቀቅ ባለድርሻ አካላት ርብርብ ሊያደርጉ እንደሚገባ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባዔ ታገሰ ጫፎ ገለጹ፡፡

የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን አፈፃፀም ላይ የተደረገ የመስክ ምልከታ ሪፖርት በዴሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ለምክር ቤቱ ቀርቧል።

አፈ ጉባዔን ጨምሮ የምክር ቤቱ ከፍተኛ የሥራ ሃላፊዎች፣ የሚዲያ ተቋማት የሥራ ሀላፊዎች እና የምክክር ኮሚሽኑ ኮሚሽነሮች በተገኙበት ሪፖርቱ ቀርቧል፡፡

በዚሁ ወቅት አፈ ጉባዔ ታገሰ ጫፎ እንደገለጹት÷ በሀገራዊ ምክክሩ ትኩረት የሚሹ ጉዳዮችን በመለየት በተፈለገው ጊዜ እንዲጠናቀቅ ባለድርሻ አካላት ርብርብ ሊያደርጉ ይገባል፡፡

ቋሚ ኮሚቴው በሲዳማ፣ በሐረሪ፣ በቤንሻጉል ጉሙዝ ክልሎች እንዲሁም በኮሚሽኑ ዋና መ/ቤት በመገኘት የምክክር ኮሚሽኑ ተግባር እና ሂደት ምን ደረጃ ላይ እንደሚገኝ ምልከታ ማድረጋቸው በሪፖርቱ ተገጿል፡፡

በቀረበው ሪፖርት መነሻነትም ውይይት እየተካሄደ መሆኑን ከህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የተገኘው መረጃ ያመላክታል፡፡