አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 17፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴዔታ አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ በኢትዮጵያ ከአሜሪካ አምባሳደር ኤርቪን ጆሴ ማሲንጋ ጋር በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይተዋል።
በውይይታቸው የጋራ በሆኑ ወቅታዊ፣ ሁለትዮሽ፣ ቀጣናዊ እና በባለብዙ ወገን ጉዳዮች ላይ መምከራቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል።
በተጨማሪም በትምህርት፣ በአቪዬሽን፣ በንግድ እና በሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት ላይ በትብብር መስራት በሚችሉባቸው ጉዳዮች ላይም መክረዋል።
በዚህ ወቅት አምባሳደር ምስጋኑ ሀገራቱ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት የጀመሩበት 120ኛ አመት ምስረታ በዓል መከበር፥ የኢትዮጵያ እና የአሜሪካ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነትን ወደ ላቀ ደረጃ ለማድረስ እንደሚያስችል ጠቁመዋል፡፡
አምባሳደር ማሲንጋ በበኩላቸው ሁነቱ የሁለቱን ሀገራት የሁለትዮሽ ግንኙነት ይበልጥ በማጠናከር ወደ ላቀ ደረጃ ለማሣደግ እንደሚረዳ ያላቸውን እምነት ገልጸዋል።
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/ ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!