የሀገር ውስጥ ዜና

የምሥራቅ አማራ ኮማንድ ፖስት የሰላምና ጸጥታ ሥራዎችን አፈጻጸም እየገመገመ ነው

By ዮሐንስ ደርበው

December 27, 2023

አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 17፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የምሥራቅ አማራ ኮማንድ ፖስት የሰላምና ጸጥታ ሥራዎችን አፈጻጸም በኮምቦልቻ ከተማ እየገመገመ ነው፡፡

ኮማንድ ፖስቱ በወቅታዊ የአካባቢው ሰላምና ደኅንነት ሁኔታዎች ላይ ግምገማ እያካሄደ መሆኑ ተገልጿል፡፡

የግምገማውን መጠናቀቅ ተከትሎም የቀጣይ አቅጣጫዎችን ያስቀምጣል ተብሎ እንደሚጠበቅ ተመላክቷል፡፡

በግምገማ መድረኩ ላይ የአማራ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አብዱ ሁሴንን ጨምሮ የኮማንድ ፖስቱ አመራሮችና ከፍተኛ የመንግስት የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/ ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!