የሀገር ውስጥ ዜና

በቁልቢና በሀዋሳ የቅዱስ ገብርኤል ዓመታዊ የንግስ በዓል በድምቀት እየተከበረ ነው

By Melaku Gedif

December 29, 2023

አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 19፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በሀዋሳና በቁልቢ የቅዱስ ገብርኤል ዓመታዊ የንግስ በዓል ብዛት ያላቸው የእምነቱ ተከታዮች፣ ቱሪስቶችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት በድምቀት እየተከበረ ነው።

በየዓመቱ ታህሳስ 19 ቀን በታላቅ ድምቀት የሚከበረው የቅዱስ ገብርኤል ዓመታዊው የንግስ በዓል በቁልቢ ገብርኤል ገዳም በተለያዩ ሃይማኖታዊ ሥነ ሥርዓቶች ታጅቦ በድምቀት እየተከበረ ነው።

በተመሳሳይ ዓመታዊው የቅዱስ ገብርኤል የንግስ በዓል በሀዋሳ ገብርኤል ገዳም በታላቅ ድምቀት እየተከበረ ይገኛል፡፡