አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 19፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ለደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ግምታዊ ዋጋው 15 ሚሊዮን ብር የሆነ የቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ፡፡
ኢንስቲትዩቱ የደህንነት መጠበቂያ ካሜራዎችና መለዋወጫዎችን ለክልሉ ፖሊስ አስረክቧል፡፡
ድጋፉ ኢንስቲትዩቱ ተቋማትን በሰውሰራሽ አስተውሎት ለመደገፍ የሚያደርገዉ ጥረት አንድ አካል እንደሆነ ተገልጿል።
ድጋፉ ግምታዊ ዋጋቸው 15 ሚሊዮን ብር የሚሆን የሰውሰራሽ አስተውሎት ካሜራዎችን ያካተተ መሆኑን ከኢንስቲትዩቱ ያገኘነው መረጃ አመልክቷል።
ኢንስቲትዩቱ ለስማርት ሀገር ግንባታ የሚያደርገዉን ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥልም ተጠቁሟል።