አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 20፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በከፍተኛ የኃላፊነት መንፈስ የነዋሪውን ፍላጎት ማርካት የሚያስችል የአመራር ቁመና ለመፍጠር ያለመ ስልጠና ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከፍተኛ አመራሮች እየተሰጠ ነው፡፡
የአስተዳደሩ ስትራቴጂክ ግቦች ተብለው ከተያዙት የብልፅግና ተምሳሌት፣ የከተማ አመራር ዘይቤ፣ ስልት እና አገልግሎት አሰጣጥን በማሻሻል ጠንካራ ተቋም መገንባት የሚሉት ይገኙበታል፡፡
ይህን መሠረት አድርጎም በስትራቴጂክ ፕሮግራሞች ከተያዙ ቁልፍ የሆነው የአመራር የአቅም ግንባታ ስራ በመሆኑ ስልጠናው መሠጠት መጀመሩን የከንቲባ ጽሕፈት ቤት መረጃ አመላክቷል፡፡
ስልጠናውም ጠንካራና የመፈጸም ብቃት ያለው ተቋማዊ አቅም መፍጠር የሚያስችል እንደሚሆን ተገልጿል፡፡
በተጨማሪም ከፍተኛ አመራሩ በንድፈ ሐሳብ የሚሰጠውን ከዕለት ተዕለት ተግባሩ ጋር እያዛመደ አቅም በመፍጠር የመካከለኛ አመራሩንና የፈጻሚውን አቅም በመገንባት አብሮ የሚሰራ የጋራ አመራር የሚሰጥ አመራር ለመፍጠር እንደሚያግዝ ተመላክቷል፡፡
እንዲሁም በከፍተኛ የኃላፊነት መንፈስ የነዋሪውን ፍላጎት ማርካት የሚያስችል የአመራር ቁመና ለመፍጠር የሚያስችል ስልጠና መሆኑ ተጠቅሷል፡፡
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/ ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!