የሀገር ውስጥ ዜና

የሶማሊላንድ ፕሬዚዳንት ሙሴቢሂ አብዲ አዲስ አበባ ገቡ

By Shambel Mihret

December 31, 2023

አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 21፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የሶማሊላንድ ፕሬዚዳንት ሙሴቢሂ አብዲ አዲስ አበባ ገብተዋል።

ፕሬዚዳንቱ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን አቀባበል አድርገውላቸዋል።

ፕሬዚዳንቱ በኢትዮጵያ በሚኖራቸው ቆይታ በተለያዩ የጋራ ጉዳዮች ዙሪያ ይወያያሉ ተብሎ ይጠበቃል።

በሳሙኤል ወርቃየሁ