የሀገር ውስጥ ዜና

ሥምምነቱ ጥበብ የተሞላ ዲፕሎማሲ፣ አብሮ የማደግ ብሂል ፣ በቅንነት እና በፈጣሪ ዕምነት የተጀመረ የዕድገት ጉዞ ሥኬት መገለጫ ነው –  የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሠ-መሥተዳድር

By Mikias Ayele

January 01, 2024

አዲስ አበባ፣ ታኅሣሥ 22፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮ -ሶማሊ ላንድ የባሕር በር ሥምምነት ጥበብ የተሞላ ዲፕሎማሲ፣ አብሮ የማደግ ብሂል ፣ በቅንነት እና በፈጣሪ ዕምነት የተጀመረ የዕድገት ጉዞ ሥኬት መገለጫ ነው ሲሉ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሠ-መሥተዳድር አቶ ጥላሁን ከበደ ገለጹ፡፡

ኢትዮጵያ የባሕር በር የምታገኝበት የመግባቢያ ሥምምነት ሠነድ በኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እና በሶማሊ ላንድ ፕሬዚዳንት ሙሴ ቢሂ አብዲ መፈረሙን ተከትሎ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሠ-መሥተዳድር አቶ ጥላሁን ከበደ የደስታ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡

ርዕሠ-መሥተዳድሩ በማኅበራዊ ትሥሥር ገፃቸው ኢትዮጵያ አሁን ባለወደብ መሆኗንም ጠቅሰው አመስግነዋል፡፡