የሀገር ውስጥ ዜና

ኢትዮጵያ የባሕር በር የምታገኝበት የመግባቢያ ሥምምነት በመፈረሙ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት የደስታ መልዕክት አስተላለፈ

By ዮሐንስ ደርበው

January 02, 2024

አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 23፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ የባሕር በር የምታገኝበት የመግባቢያ ሥምምነት በመፈረሙ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት የደስታ መልዕክት አስተላለፈ።

የጠቅላይ ሚኒስቴር ጽ/ቤት አመራሮችና ሰራተኞች የስምምነት ሠነዱ መፈረሙን አስመልክቶ የደስታ መግለጫ ስነ-ስርዓት አካሂደዋል።

በስነ-ስርዓቱም የኢፌድሪ መንግስት እና የሶማሌላንድ መንግስት የፈረሙት የትብብር እና የአጋርነት መግባቢያ ሠነድን በተመለከት የ’እንኳን ደስ ያለን’ መልእክታቸውን አስተላልፈዋል።