የሀገር ውስጥ ዜና

የሁለቱ ም/ቤቶች አፈ-ጉባዔዎች በሀገር አቀፍ የሕግ አውጪዎች መድረክ ለመታደም ወደ ሐረር አቀኑ

By ዮሐንስ ደርበው

January 02, 2024

አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 23፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ-ጉባዔ ታገሰ ጫፎ እና የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ-ጉባዔ አገኘሁ ተሻገር ነገ በሐረር ከተማ በሚጀመረው ሀገር አቀፍ የሕግ አውጪዎች የጋራ መድረክ ላይ ለመታደም ወደ ሥፍራው አቅንተዋል፡፡

ከሁለቱ ምክር ቤቶች አፈ-ጉባዔዎች በተጨማሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ከፍተኛ አመራሮች፣ የክልል ምክር ቤቶች አፈ ጉባዔዎች እና ከፍተኛ አመራሮችም በመድረኩ እንደሚታደሙ ተገልጿል፡፡

የመድረኩ ተሳታፊዎችም ዛሬ ድሬዳዋ ከተማ ሲገቡ÷ የሐረሪ ክልል ምክር ቤት አፈ ጉባዔ ሱልጣን አብዱሰላም፣ የሐረሪ ጉባዔ አፈ ጉባዔ አቶ መህየዲን አሕመድ፣ የድሬዳዋ ምክር ቤት አፈ-ጉባዔ ፈቲያ አደን እና ሌሎች ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች አቀባበል አድርገውላቸዋል መባሉን የሐረሪ ክልል ኮሙኒኬሽን መረጃ አመላክቷል፡፡#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- FBC(Fana Broadcasting Corporate S.C.) ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/ ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!