አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 24፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) እንደ ሀገር አብሮነትን በዘላቂነት ለመገንባት አስተሳሳሪ ትርክቶችን መገንባት ያስፈልጋል ሲሉ የብልፅግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ አደም ፋራህ ገለጹ፡፡
“ብዝሃነትን መኖር” በሚል መሪ ሃሳብ ሀገር አቀፍ የአብሮነት ቀን በመከበር ላይ ይገኛል።
በብልጽግና ፓርቲ ዋና ጽ/ቤት “አብሮነትን ለማጠናከር የሚተጋ አመራር” በሚል መሪ ሃሳብ መርሐ ግብሩ ተካሂዷል።
በመርሐ ግብሩ ላይ መልዕክት ያስተላለፉት አቶ አደም ፋራህ÷ በዓሉን በስፖርታዊ እንቅስቃሴ ማክበር ያስፈለገበት ዋነኛው ምክንያት ስለ አብሮነት ፋይዳ ግንዛቤ ለመፍጠር በማለም እንደሆነ አንስተዋል።
እንደ ሀገር አብሮነትን በዘላቂነት ለመገንባት አስተሳሳሪ ትርክቶችን መገንባት ጠቃሚ መሆኑንና የተናጠልነት ክፍተትን ለመሙላት እጅግ ጠቃሚ መሳሪያ መሆኑንም ገልፀዋል።
ድህነት፣ ኋላ ቀርነት፣ ጦርነት ከአብሮነት መላላት ጋር የሚመጡ ችግሮች መሆናቸውን ያነሱት አቶ አደም÷ ለእነዚህ ጉዳዮች በዘላቂነት እልባት መስጠት እንዲቻል የአብሮነትን ባህል መገንባት እንደሚያስፈልግ አብራርተዋል።
አብሮነት ለሀገራችን ትልቅ ትርጉም ያለውና ያሳካናቸው ድሎች ልዩነታችንን በመተው በጋራ በመቆማችን የተገኙ እንደሆኑ የአድዋ ድል ሁነኛ ምስክር ነው ሲሉ አንስተዋል።
ይህንን የአሰባሳቢነት ትርክት መገለጫ የሆነው የአብሮነት ሀሳብን መሰረት ለማስያዝም ስፖርት ሁነኛ መሳሪያ መሆኑን ነው የጠቀሱት።
መላው የብልፅግና ፓርቲ አመራርና አባላቶችም ይህ አዎንታዊ ሀሳብ በዘላቂነት የታለመለትን ግብ ይመታ ዘንድ የበኩላቸውን አስተዋፆ እንዲያበረክ