አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 24፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) 3ኛው የማህበረሰብ አቀፍ የአካል ብቃት እንቅቃሴ በሁሉም ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች ዛሬ ተካሂዷል።
”የአንድ ሰዓት የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ለሚሊዮኖች” በሚል መሪ ሀሳብ የተካሄደው የአካል ብቃት እንቅስቃሴ መርሃ ግብር ህብረተሰቡ ማህበራዊ ትስስሩን እንዲያጠናክርና አብሮነቱን እንዲያዳብር ያለመ መሆኑ ተገልጿል።
መርሃ -ግብሩ በሁሉም የሀገሪቱ ክፍሎች የተካሄደ ሲሆን ሁሉም በያለበት ስፍራ እንዲሁም በተመረጡ የክልል ማዕከላት ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች በተሳተፉበት ተካሂዷል።
በዚህም ለ1 ሰዓት ያህል በተደረገው የአካል ብቃት እንቅስቃሴ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ዜጎች መሳተፋቸው ተነግሯል።
የማህበረሰብ አቀፍ የአካል ብቃት ስፖርትን ባህሉ ያደረገ በአካል እና በአዕምሮ የጎለበተ ማህበረሰብ ለመፍጠር ትልቅ አበርክቶ እንዳለውም ተገልጿል።