የሀገር ውስጥ ዜና

ሁሉም ኢትዮጵያውያን በባህር በር ጉዳይ የበኩላቸውን አስተዋፅዖ ሊያደርጉ ይገባል ተባለ

By ዮሐንስ ደርበው

January 03, 2024

አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 24፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ሁሉም ኢትዮጵያዊ ዜጋ ከፖለቲካ አመለካከት ልዩነት ወጥቶ በባህር በር ጉዳይ የበኩሉን አስተዋፅዖ ሊያደርግ እንደሚገባ የውሃ እና ኢነርጂ ሚኒስትሩ ሀብታሙ ኢተፋ (ዶ/ር ኢ/ር) ተናገሩ፡፡

የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር እና ተጠሪ ተቋማት ከፍተኛ አመራሮችና ባለሙያዎች ኢትዮጵያ የባህር በር ለማግኘት የሚያስችላትን ስምምነት ከሶማሊላንድ ጋር መፈረሟን አስመልክቶ የተሰማቸውን ደስታ ገልፀዋል፡፡

በፕሮግራሙ የተገኙት ሚኒስትሩ፥ኢትዮጵያ በታሪኳ የባህር በርን በመጠቀም ከዓለም ማህበረሰብ ጋር የምታደርጋቸው የንግድና ሌሎች ግንኙነቶች እንደነበሩ አስታውሰዋል፡፡

በተለያየ ጊዜ ባጋጠሙ ፖለቲካዊ ችግሮች ኢትዮጵያ ከውሃ አካላት እንድትርቅ ተደርጓል ያሉት ሚኒስትሩ÷ አሁን ላይ ከሶማሌ ላንድ ጋር እጅግ ሰላማዊ በሆነ መንገድ እና ብስለት በተሞላበት የአመራር ጥበብ ወደ ባህር በር መጠጋታችን ትልቅ ኩራት ነው ብለዋል፡፡

በመሆኑም ማንኛውም ኢትዮጵዊ ከፖለቲካዊ አመለካከት ወጥቶ በባህር በር ጉዳይ የበኩሉን አስተዋፅዖ ሊያደርግ እንደሚገባ ሚኒስትሩ መናገራቸውን የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል፡፡

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- FBC(Fana Broadcasting Corporate S.C.) ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/ ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!