የሀገር ውስጥ ዜና

የተለያዩ ሀገራት ኤምባሲዎች የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ

By Meseret Awoke

January 06, 2024

አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 27፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ የሚገኙ የተለያዩ ሀገራት ኤምባሲዎች ለኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

በኢትዮጵያ የአውስትራሊያ አምባሳደር ጁሊያ ሮበርት፥ ገናን (የኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓልን) ለሚያከብሩ ኢትዮጵያውያን መልካም በዓል ሲሉ ተመኝተዋል፡፡

ባለፈው ዓመት የገና በዓልን ምክንያት በማድረግ ላሊበላን መጎብኘታቸውን ገልጸው ፥ በሺዎች የሚቆጠሩ የበዓሉ ታዳሚዎች በተገኙበት ድንቅ የሆነ የሃይማኖታዊ የበዓል አከባበርን ተመልክቻለሁ ብለዋል፡፡

የስዊድን ኤምባሲም ለመላው የክርስትና እምነት ተከታይ ኢትዮጵያውያን መልካም በዓል ሲል ምኞቱን ገልጿል፡፡

የሩሲያ ኤምባሲ በበኩሉ የገና በዓልን ምክንያት በማድረግ ባስተላለፈው መልዕክት፥ ለመላው የክርስትና እምነት ተከታይ ኢትዮጵያውያን የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፏል፡፡

ኤምባሲው አክሎም ለመላ ኢትዮጵያውያን ጤና፣ ደስታና ሰላምን ተመኝቷል።

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- FBC (Fana Broadcasting Corporate S.C.) ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/ ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!