የሀገር ውስጥ ዜና

የሞተር ሳይክሎች እና ከባድ ተሸከርካሪዎች ክልከላ የተደረጉባቸው መንገዶች ይፋ ሆኑ

By Mikias Ayele

January 07, 2024

አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 28፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ሞተር ሳይክሎችና ከሁለት ቶን በላይ የሆኑ ከባድ ተሽከርካሪዎች መንቀሳቀስ የመይችሉባቸውን መንገዶችን  የአዲስ አበባ ፖሊስ ይፋ አደርጓል ።

መንግዶቹ ቦሌ – በኦሎምፒያ – መስቀል አደባባይ – ብሔራዊ ቤተ -መንግሥት  እንዲሁም አራት ኪሎ በሁለቱም አቅጣጫ መሆናቸው ተገልጿል፡፡

በመሆኑም የሞተር ሳይክል እና የከባድ መኪና አሽከርካሪዎች  ከላይ በተጠቀሱት መንገዶች ከታህሳስ 29 ቀን 2016 ዓ/ም ጀምሮ መንቀሳቀስ እንደማይችሉ አውቀው ሌሎች አማራጭ መንገዶችን እንዲጠቀሙ  የአዲስ አበባ ፖሊስ  አሳስቧል።

በመንግዶቹ ክልከላውን የሚገልፁ ምልክቶች መተከላቸውን ያስታወቀው ፖሊስ የተላለፈውን መልዕክት በማያከብሩ  አሽከርካሪዎች ላይ ህጋዊ  እርምጃ እንደሚወስድ አስታውቋል፡፡