የሀገር ውስጥ ዜና

የሀርቡ ነዋሪዎች ኢትዮጵያ የባሕር በር ለማግኘት የሚያስችላትን ስምምነት በመፈረሟ ደስታቸውን ገለጹ

By ዮሐንስ ደርበው

January 08, 2024

አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 29፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በደቡብ ወሎ ዞን የሀርቡ ከተማ ነዋሪዎች ኢትዮጵያ የባሕር በር ለማግኘት የሚያስችላትን ስምምነት ከሶማሊላንድ ጋር በመፈራረሟ በአደባባይ በመውጣት የተሰማቸውን ደስታ ገልጸዋል፡፡

በድጋፍ ሰልፉ የተገኙት የከተማዋ ነዋሪዎችም ኢትዮጵያ የባሕር በር ለማግኘት የሚያስችላትን ስምምነት በመፈራረሟ ደስታ እንደተሰማቸው ገልጸዋል፡፡

“ስምምነቱ ሀገራዊ ሥኬታችንን ለማፋጠን ይረዳል” ማለታቸውን የደቡብ ወሎ ዞን ኮሙኒኬሽን መምሪያ መረጃ አመላክቷል፡፡

ይህ ስኬት የተገኘው በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በሳል የዲፕሎማሲ ጥረት በመሆኑ ምስጋና ይገባቸዋልም ብለዋል ነዋሪዎቹ፡፡

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- FBC (Fana Broadcasting Corporate S.C.) ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/ ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!