የሀገር ውስጥ ዜና

የወንጪ-ደንዲ ኢኮ ቱሪዝም መንደር ተመረቀ

By Tamrat Bishaw

January 13, 2024

አዲስ አበባ፣ ጥር 4፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የወንጪ-ደንዲ ኢኮ ቱሪዝም መንደር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት በዛሬው ዕለት ተመርቋል፡፡

ከጠቅላይ ሚኒስትሩ በተጨማሪም የአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ሙሳ ፋኪ ማኅማት፣ የኢጋድ ሊቀመንበር ወርቅነህ ገበየሁ (ዶ/ር) እና ሌሎች የዲፕሎማቲክ ልዑካን ቡድን አባላት እንዲሁም የፌዴራልና የክልል ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡

የወንጪ-ደንዲ ኢኮ ቱሪዝም መንደር በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ‘ገበታ ለሀገር’ መርሐ ግብር ከተገነቡት መዳረሻዎች ሶስተኛው መሆኑን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት መረጃ ያመላክታል፡፡