የሀገር ውስጥ ዜና

አንጋፋው ጋዜጠኛ አስፋው መሸሻ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ

By Mikias Ayele

January 14, 2024

አዲስ አበባ፣ ጥር 5፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) አንጋፋው ጋዜጠኛ አስፋው መሸሻ ባደረበት ህመም በአሜሪካ ሕክምናውን ሲከታተል ቆይቶ በዛሬው ዕለት ሕይወቱ አልፏል፡፡

ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ለቤተሰቦቹ እና ወዳጅ ዘመዶቹ መጽናናትን ይመኛል።