የሀገር ውስጥ ዜና

የቀዳማይ ልጅነት ልማት ፕሮግራምን ለማገዝ የሚያስችል ስምምነት ተፈረመ

By Feven Bishaw

January 16, 2024

 

አዲስ አበባ፣ ጥር 7፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ “የቀዳማይ ልጅነት ልማት ፕሮግራም“ ለማገዝ የሚያስችል የመግባቢያ ስምምነት ከተባበሩት መንግስታት የህፃናት አድን ድርጅት(ዩኒሴፍ) ጋር ተፈራርመዋል።

ከንቲባዋ በማህራዊ ትስስር ገፃቸው÷” ከዩኒሴፍ የኢትዮጵያ ተወካይ አቡበክር ካምፖ(ዶ/ር) ጋር የተፈራረምነው የመግባቢያ ስምምነት ከገነባናቸው የሕጻናት መዋያ እንዲሁም የመጫወቻና መዝናኛ ማዕከላት በተጨማሪ የሕጻናት የጤና አገልግሎት ማሻሻያ ላይ እያደረግን ያለውን ስራ የሚያግዝ ይሆናል”ብለዋል።

አዲስ አበባን ሕጻናት ቦርቀው፣ በአካልና በአዕምሮ ተገንብተው የሚያድጉባት ምርጥ አፍሪካዊት መዲና ለማድረግ በትጋት መስራታችንን እንቀጥላለን ሲሉም አክለዋል፡፡