የሀገር ውስጥ ዜና

6 ኢትዮጵያዊያን ህጻናት ነጻ የልብ ቀዶ ሕክምና ለማድረግ ወደ እስራኤል አቀኑ

By Melaku Gedif

January 17, 2024

አዲስ አበባ፣ ጥር 8፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ስድስት የልብ ህሙማን ኢትዮጵያዊያን ሕጻናት ነጻ የልብ ቀዶ ሕክምና ለማድረግ ከእናቶቻቸው ጋር ወደ እስራኤል አቅንተዋል፡፡

የሕክምና ወጪውም ‘ሴቭ ኤ ቻይልድ’ስ ኸርት’ በተሰኘ የእስራኤል ግብረ ሰናይ ድርጅት እንደሚሸፈን የእስራኤል ኤምባሲ መረጃ ያመለክታል፡፡

እስራኤል በተለያዩ ዘርፎች ለኢትዮጵያ የምታደርገውን ድጋፍ አጠናክራ እንደምትቀጥልም ተጠቁሟል፡፡

#Ethiopia ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡ (FBC (Fana Broadcasting Corporate S.C.) ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/ ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!