የሀገር ውስጥ ዜና

በጋምቤላ ክልል የጥምቀት በዓል እሴቱን ጠብቆ በሰላም እንዲከበር ቅድመ ዝግጅት ተጠናቀቀ

By ዮሐንስ ደርበው

January 17, 2024

አዲስ አበባ፣ ጥር 8፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በጋምቤላ ክልል የከተራና የጥምቀት በዓል እሴቱን ጠብቆና ያለምንም የፀጥታ ስጋት እንዲከበር አስፈላጊው ቅድመ ዝግጅት መጠናቀቁን የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ።

በዓሉ በክልሉ በድምቀትና ከፀጥታ ስጋት ነፃ ሆኖ እንዲከበር ኮሚቴ ተዋቅሮ ስምሪት መደረጉን የኮሚሽኑ ኮሚሽነር ኡሞድ ኡሞድ ተናግረዋል፡፡

በበዓሉ ወቅት ችግሮች ቢከሰቱ አፋጣኝ ምላሽ ለመስጠት መርማሪ ፖሊስን፣ ዐቃቤ ሕጎችንና ዳኞችን ያካተተ ፈጣን ችሎት መቋቋሙን ለኢዜአ ገልጸዋል፡፡

በዓሉ በሚከበርበት ወቅት የፀጥታ ችግሮች ካጋጠመ ሕብረተሰቡ ለፀጥታ አካል ጥቆማ እንዲያደርግ ጠይቀዋል፡፡