የሀገር ውስጥ ዜና

በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳይ ላይ ለአምባሳደሮች ማብራሪያ ተሰጠ

By ዮሐንስ ደርበው

January 17, 2024

አዲስ አበባ፣ ጥር 8፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በተለያዩ ሀገራት ኢትዮጵያን እያገለገሉ ለሚገኙ አምባሳደሮች እና በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ለሚገኙ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳይ ላይ ማብራሪያ ተሰጥቷል፡፡

ማብራሪያውን የሠጡት÷ የፍትሕ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር)፣ የጠቅላይ ሚኒስትሩ ብሔራዊ ደኅንነት አማካሪ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን እና የብሔራዊ ተሃድሶ ኮሚሽን ኮሚሽነር አምባሳደር ተሾመ ቶጋ ናቸው፡፡

ማብራሪያውም በኢትዮጵያ ወቅታዊ ጉዳዮች፣ ሠላም እና ጸጥታ፣ በሽግግር ፍትሕ እና የቀድሞ ታጣቂዎችን መልሶ በማቋቋም ሂደት ላይ ያተኮረ መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ አመላክቷል፡፡