የሀገር ውስጥ ዜና

ወደ ሀገር ቤት ለገቡ 2ኛ ትውልድ ኢትዮጵያውያን የአቀባበል መርሐ ግብር ተካሄደ

By Shambel Mihret

January 18, 2024

አዲስ አበባ፣ ጥር 9፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድን (ዶ/ር) ጥሪ ተቀብለው ወደ ሀገር ቤት ለገቡ ኢትዮጵያውያን ይፋዊ የአቀባበል መርሐ ግብር በወዳጅነት አደባባይ ተካሂዷል፡፡

በመርሐ ግብሩ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ፣ ከአሜሪካ፣ አውሮፓና ሌሎችም የዓለም ክፍሎች የመጡ ሁለተኛ ትውልድ ኢትዮጵያውያን፣ የስራ ኃላፊዎችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

ከንቲባ አዳነች በዚሁ ወቅት እንደገለፁት ÷ ሁለተኛ ትውልድ ኢትዮጵያውያን በሀገር ቤት የሚያደርጉት ቆይታ ስኬታማ እንዲሆን የተለያዩ ተግባራት በቅንጅት እየተሰሩ ነው፡፡

ሀገራቸውን የሚጎበኙበትና ታሪክና ባህላቸውን የሚያውቁበት ልዩ ልዩ መርሐ ግብር መዘጋጀቱንም ነው የጠቀሱት።

ሁለተኛ ትውልድ ኢትዮጵያውያኑ በመዲናዋ በድምቀት በሚከበረው የከተራና የጥምቀት በዓል፣ የአፍሪካ ህብረት ጉባኤ እና የአድዋ ድል በዓል ላይ እንዲገኙና እንዲሳተፉም ጥሪ ማቅረባቸውን የዘገበው ኢዜአ ነው፡፡