የሀገር ውስጥ ዜና

የከተራ በዓል በባቱ ከተማ ተከበረ

By ዮሐንስ ደርበው

January 19, 2024

አዲስ አበባ፣ ጥር 10፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የከተራ በዓል በባቱ ከተማ ደምበል ደሴቶች ተከብሯል፡፡

በደሴቶቹ የሚገኘው የገሊላ ካህናት ሰማይ ተክለ ሃይማኖት ታቦትና በደብረ ሲና ደሴት የምትገኘው የቅድስት ማርያም ገዳም ታቦታት ከጫሳ ቅዱስ ሚካኤል ገዳም ጋር ሆነው በጥምቀተ ባሕሩ ያድራሉ፡፡

ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ያነጋገራቸው የበዓሉ ታዳሚዎች እንዳሉት÷ ታቦታቱን በጀልባ ማጀብ ልዩ ስሜት ይፈጥራል፡፡

በጥላሁን ይልማ