የሀገር ውስጥ ዜና

የጥምቀት በዓል በኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ተከበረ

By Shambel Mihret

January 20, 2024

አዲስ አበባ፣ ጥር 11፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የጥምቀት በዓል በኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን በተለያዩ ሃይማኖታዊ ስነ-ስርአቶች ተከበረ፡፡

በልደታ ማሪያም ካቶሊካዊት ካቴድራል ቤተክርስቲያን በዓሉ በቅዳሴ፣ በዝማሬ እና በፀሎት ነው የተከበረው።

ጥምቀት ትህትና የታየበት፣ ሀጢያት የተሰረየበት የመንፈስ ቅዱስ ብርሃን የተገለጠበት በዓል በመሆኑ በዓሉ አምላክን በማመስገን በፀሎት ተከብሮ ይውላል።

በዓሉ በመላው ሀገሪቱ ባሉ የካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን በኢትዮጵያ ስርዓት ተከብሮ ይውላል።

በአከባበር ሥነ-ሥርዓቱም የቅዳሴ ስርዓት የተከናወነ ሲሆን÷ምእመናኑን ፀበል የማጥመቅ ስነ ስርዓትም መርሐ ግብርም ተካሂዷል።

በትዕግስት ብርሀኔ

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/ ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!