የሀገር ውስጥ ዜና

አርብቶ አደሩ ሀብቱን በአግባቡ እንዲጠቀም መሥራት እንደሚገባ ተመለከተ

By ዮሐንስ ደርበው

January 22, 2024

አዲስ አበባ፣ ጥር 13፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) አርብቶ አደሩ ያለውን ሀብት በአግባቡ እንዲጠቀም በቅንጅት መሥራት እንደሚገባ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ብሔረሰቦች ምክር ቤት አፈ-ጉባዔ አስገነዘቡ፡፡

የአርብቶ አደሮች ቀን በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ለመጀመሪያ ጊዜ ተከብሯል፡፡

አፈ-ጉባዔ መቱ አኩ በአከባበሩ ላይ ባደረጉት ንግግር አርብቶ አደሩ ካለው ሀብት ሳይጠቀም መቆየቱን ጠቅሰው÷ አሁን ግን ሀብቱን በአግባቡ እንዲጠቀም በትኩረት መሥራት ይገባል ብለዋል፡፡

ለዚህም የአርብቶ አደሩን የእርስ በርስ ትስስር ማጠናከርና በልማት ማስተሳሰር ቁልፍ ጉዳይ መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡

የክልሉ አርብቶ አደርና ቆላማ አካባቢ ቢሮ ኃላፊ ታምሩ ቦኒ÷ አርብቶ አደሩ ያለውን ሀብት በአግባብ እንዳይጠቀም እንቅፋት የሆኑትን የፀጥታ ችግሮች መቅረፍ እንደሚገባ አስገንዝበዋል፡፡

በፍሬው ዓለማየሁ