የሀገር ውስጥ ዜና

የብልጽግና ፓርቲ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ስብሰባውን ማካሄድ ጀመረ

By ዮሐንስ ደርበው

January 22, 2024

አዲስ አበባ፣ ጥር 13፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የብልጽግና ፓርቲ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ስብሰባውን ማካሄድ ጀምሯል፡፡

የብልጽግና ፓርቲ ፕሬዚዳንት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በማኅበራዊ ትሥሥር ገጻቸው እንደገለጹት÷ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴው በዐበይት ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ይወያያል፡፡

በተጨማሪም በልዩ ልዩ የፓርቲ አጀንዳዎች ላይም እንደሚመክር አመላክተዋል፡፡