የሀገር ውስጥ ዜና

የአማራ ክልል ገቢዎች ቢሮ 17 ነጥብ 1 ቢሊየን ብር በላይ ገቢ ሰበሰበ

By Mikias Ayele

January 22, 2024

አዲስ አበባ፣ ጥር 13፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ባለፉት ስድስት ወራት 17 ነጥብ 1 ቢሊየን ብር  በላይ ገቢ መሰብሰቡን የአማራ ክልል ገቢዎች ቢሮ አስታውቋል።

በግማሽ ዓመቱ ከተለያዩ ምንጮች የሚገኘውን ገቢ ለማሳደግ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በቅንጅት መሰራቱን  የቢሮው መረጃ ያመላክታል፡፡

በዚህም ከመደበኛ ግብር ከፋዮች እና መዘጋጀ ቤት አገልግሎት 17 ነጥብ 1 ቢሊየን ብር በላይ ገቢ መሰብሰብ መቻሉ ተጠቁሟል፡፡