የሀገር ውስጥ ዜና

ጋዜጠኛ ገነነ መኩሪያ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ

By ዮሐንስ ደርበው

January 23, 2024

አዲስ አበባ፣ ጥር 14፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ጋዜጠኛ ገነነ መኩሪያ (ሊብሮ) ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል።

ገነነ መኩሪያ ባደረበት ህመም ምክንያት በሕክምና ሲረዳ ቆይቶ ሕይወቱ ዛሬ ንጋት ላይ ማለፉን ቤተሰቦቹ አስታውቀዋል፡፡