አዲስ አበባ፣ ጥር 14፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ የአሜሪካ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ አምባሳደር ማይክ ሀመርን በጽሕፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል።
አምባሳደር ምስጋኑ በዚህ ወቅት እንዳሉት ኢትዮጵያና አሜሪካ ዘመናትን ያስቆጠረ ግንኙነት ያላቸው አጋር ሀገራት ናቸው።
እንዲሁም ኢትዮጵያ ዘላቂ ሰላምን በመገንባት ረገድ እያከናወነ ያለውን ተግባር በተመለከተ ገለጻ አድርገዋል።
ሁለቱ ወገኖች በአህጉራዊና ዓለም አቀፋዊ የጋራ ጉዳዮች ዙሪያ መምከራቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያመለክታል።