አዲስ አበባ፣ ጥር 15፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በተጠናቀቀው ግማሽ ዓመት ከ630 ሜትሪክ ቶን በላይ ምርቶች ከደረጃ በታች በመሆናቸው ምክንያት ወደ ሀገር ውስጥ እንዳይገቡ ማድረጉን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡
የ5 ሺህ 713 አስመጪዎችን ጥያቄ በመቀበል ከ1 ሚሊየን 868 ሺህ ሜትሪክ ቶን በላይ አስገዳጅ ደረጃ የወጣላቸው የገቢ ዕቃዎች ላይ የጥራት ቁጥጥር ሥራ ማከናወኑንም ነው ሚኒስቴሩ የገለጸው፡፡
በዚህም 630 ነጥብ 21 ቶን የተለያየ የምግብ ውጤት፣ የኮንስትራክሽንና የኬሚካል ውጤት ላይ በተደረገ የላቦራቶሪ ፍተሻ እና የኢንስፔክሽን ሥራ ከደረጃ በታች መሆናቸው ተረጋግጦ ወደ ሀገር ውስጥ እንዳይገቡ ታግደዋል ነው የተባለው፡፡
በቀጣይም የጥራት ማረጋገጥ ሥራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ተመላክቷል፡፡
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/ ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!