የሀገር ውስጥ ዜና

አቶ ተመስገን ጥሩነህ የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት ሆነው ተመረጡ

By Melaku Gedif

January 26, 2024

አዲስ አበባ፣ ጥር 17፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የብልጽግና ማዕከላዊ ኮሚቴ አቶ ተመስገን ጥሩነህን የፓርቲው ምክትል ፕሬዚዳንት አድርጎ መርጧል፡፡

የብልጽግና ማዕከላዊ ኮሚቴ የፓርቲውን የአመራር የመተካካት መርህንና የአሰራር ሥርዓት በመከተል ዛሬ ባካሄደው የማጠቃለያ ስብሰባ በሙሉ ድምፅ አቶ ደመቀ መኮንን በክብር ሸኝቷል፡፡

በምትካቸውም የፓርቲው ሥራ አስፈጻሚ የነበሩትን አቶ ተመስገን ጥሩነህን ምክትል ፕሬዚዳንት አድርጎ በአብላጫ ድምጽ መርጧል።