የሀገር ውስጥ ዜና

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) በጣልያን-አፍሪካ ጉባዔ ላይ እየተሳተፉ ነው

By Melaku Gedif

January 29, 2024

አዲስ አበባ፣ ጥር 20፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከሌሎች የአፍሪካ መሪዎች ጋር በጣልያን ጠቅላይ ሚኒስትር ጂዮርጂያ ሜሎኒ አስተናጋጅነት በተሰናዳው የጣልያን-አፍሪካ ጉባዔ እየተሳተፉ ነው፡፡

ጉባዔው የጋራ እድገት ድልድይ በሚል መሪ ሀሳብ ነው እየተካሄደ የሚገኛው፡፡

በጉባዔው ‘ማቲዬ ፕላን ፎር አፍሪካ’ የተሰኘው የጣልያን ዕቅድ ቀርቦ ውይይት እንደሚካሄድበት የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት መረጃ ያመላክታል፡፡