አዲስ አበባ፣ ግንቦት 25፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በኢትዮጵያ 29 የኮሮና ቫይረስ መመርመሪያ ማእከላት አገልግሎት በመስጠት ላይ መሆናቸውን የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ።
በኢትዮጵያ የኮሮና ቫይረስ በሽታ የላብራቶሪ ምርመራ ባለመኖሩ ወደ ደቡብ አፍሪካ ናሙናዎችን እየተላከ ውጤቱን ለማወቅ የጊዜና የገንዘብ ወጪ ያስክትል እንደነበር ያስታወሰው ሚኒስቴሩ፥ ይህን ችግር በመረዳት በአጭር ጊዜ በሀገር ውስጥ የመመርመሪያ መሳሪዎችን በሟሟላት እና ባለሙያዎችን በማሰልጠን የላብራቶሪ ምርመራ ማዕከላትን ማደራጀቱን አስታውቋል።