የሀገር ውስጥ ዜና

ከዓድዋ ድል ጋር የተያያዙ ቅርሶች ለመዲናዋ አሥተዳደር ተበረከተ

By Feven Bishaw

January 30, 2024

 

 

አዲስ አበባ፣ ጥር 21፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ተወካዮች ከዓድዋ ድል ጋር የተያያዙ ቅርሶችን ለአዲስ አበባ ከተማ አሥተዳደር አበርክተዋል፡፡

ከዓድዋ ድል ጋር የተያያዙ ቅርሶች በዓድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም እንዲቀመጡ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ያቀረቡትን ጥሪ ተከትሎ ነው ተወካዮቹ ቅርሶቹን ያስረከቡት፡፡

ክልሉ ያሰባሰባቸውን ከዓድዋ ድል ጋር የተያያዙ ቅርሶች ለአሥተዳደሩ በማስረከቡ የከንቲባ ጽሕፈት ቤትና የካቢኔ ጉዳዮች ኃላፊ ጥላሁን ወርቁ አመስግነዋል፡፡

ከዓድዋ ድል ጋር የተያያዙ ቅርሶች ትውልድ እንዲማርባቸው በዓድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም እንዲቀመጡ ሌሎች ክልሎችም አስተዋጽኦ እንዲያበረክቱ ጥሪ መቅረቡን የከንቲባ ጽሕፈት ቤት መረጃ አመላክቷል፡፡