የሀገር ውስጥ ዜና

የሰላም ጥሪውን ተቀብለው ወደ ተሃድሶ ስልጠና ለገቡ ሰልጣኞች አቀባበል ተደረገ

By Melaku Gedif

January 31, 2024

አዲስ አበባ፣ ጥር 22፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የአማራ ክልል መንግስት ያቀረበውን የሰላም ጥሪ ተቀብለው ወደ ተሃድሶ ስልጠና ለገቡ ሰልጣኞች የእንኳን ደህና መጣችሁ አቀባበል ተደርጓል፡፡

በሥነ-ሥርዓቱ ላይ የክልሉ የሰላምና ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ አቶ ደሳለኝ ጣሰው፣ የምስራቅ ዕዝ አዛዥ ሌ/ጀ መሃመድ ተሰማ እና የሰሜን ምዕራብ ዕዝ አዛዥ ሌ/ጀ ብርሀኑ በቀለ ተገኝተዋል።

አቶ ደሳለኝ ጣሰው በዚህ ወቅት÷ የተሃድሶ ሰልጣኞች ውግንናችሁን ለህገ-መንግስቱ እና ለህዝብ መሆኑን አምናችሁና ተቀብላችሁ ስለመጣችሁ እንኳን ደስ አላችሁ ብለዋል፡፡

ሌ/ጀ ብርሀኑ በቀለ በበኩላቸው÷ ሀገርና ህዝብን ለመካስ ዳግመኛ ያገኛችሁትን ዕድል በአግባቡ በመጠቀም ለሀገራችሁ ዘብ መቆም አለባችሁ ሲሉ አሳስበዋል፡፡

የተሃድሶ ሰልጣኞች የክልሉን ህዝብ እንዲሁም ሀገራቸውን ለመጠበቅ ቃል መግባታቸውንም የአማራ ክልል ፖሊስ መረጃ ያመላክታል፡