የሀገር ውስጥ ዜና

መሰቦ ሲሚንቶ ፋብሪካ በትግራይ ክልል በድርቅ ለተጎዱ ወገኖች የ50 ሚሊየን ብር ድጋፍ አደረገ

By Shambel Mihret

February 01, 2024

አዲስ አበባ፣ ጥር 23፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) መሰቦ ሲሚንቶ ፋብሪካ በትግራይ ክልል በድርቅ ለተጎዱ ወገኖች የሚውል የ50 ሚሊየን ብር ድጋፍ አድርጓል፡፡

የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር በክልሉ የተለያዩ አካባቢዎች ድርቅ ማጋጠሙን ተከትሎ በድርቁ ምክንያት ጉዳት ላጋጠማቸው ወገኖች ድጋፍ እንዲደረግ ጥሪ ማቅረቡ ይታወሳል፡፡

በዚህም የፌደራል መንግስት ተቋትን ጨምሮ የተለያዩ አካላት ድጋፍ እያደረጉ ይገኛል።

መሰቦ ሲሚኒቶ ፋብሪካም በክልሉ ላጋጠመው ድርቅ የ50 ሚሊየን ብር ድጋፍ ማበርከቱን ከፋብሪካው የተገኘው መረጃ ያመላክታል፡፡