አዲስ አበባ፣ ጥር 23፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ በታይላንድ ባንኮክ እየተካሄደ ባለው 25ኛው የዓለም የወደፊት ገበያ ዓመታዊ ጉባኤ ላይ እየተሳተፈች ነው፡፡
የንግድ እና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ዴኤታ ካሳሁን ጎፌ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው÷25ኛው የዓለም የወደፊት ገበያ ዓመታዊ ጉባኤ በታይላንድ ባንኮክ መካሄድ መጀመሩን ገልጸዋል፡፡
ኢትዮጵያም የጉባኤው አባል ሀገር ከሆነች ሁለተኛ ዓመቷን እንደያዘች በመግለጽ፤ በጉባኤው መሳተፏ መልካም ተሞክሮዎችን ቀምራ ዘመናዊ የወደፊት ገበያ እንዲኖራት ያስችላል ነው ያሉት፡፡
ጉባኤው ከሚመክርባቸ ጉዳዮች መካከል ስለ ካፒታል ገበያ አብዮት እና ዘላቂ እድገት፣ የወደፊት ኢንዱስትሪዎች ቀጣናዊ አዝማሚያ፣ የዓለም ተለዋዋጭ የንግድ ከባቢ በቀጣና እና ሀገራት ገበያ ላይ የሚያሳድረው ተፅእኖ እንዲሁም ሌሌች ጉዳዮች ይዳሰሳሉ ብለዋል፡፡