አዲስ አበባ፣ ጥር 24፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ታጣቂ ኃይሎች የሰላምን ጥሪ ተቀብለው የዜጎችን ህይወት በሚለውጥ ስራ ሊሰማሩ ይገባል ሲሉ ምሁራን ገለጹ።
በወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካል ሳይንስና ዓለም አቀፍ ግንኙነት መምህሩ በቃሉ አጪሶ እና በአሶሣ ዩኒቨርሲቲ የማህበራዊ ሳይንስ መምህርና ዲን የሆኑት አበበ አኖም(ዶ/ር) ከፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ጋር ቆይታ አድርገዋል፡፡
ምሁራኑ መንግስት ያቀረበው የሰላም ጥሪ ትልቅ የፖለቲካ እርምጃ በመሆኑ በቀላሉ ሊታይ የሚገባ አይደለም ብለዋል።
በወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካል ሳይንስና ዓለም አቀፍ ግንኙነት መምህሩ በቃሉ አጪሶ እንዳሉት ፥ ማንኛውም ኃይል ለሰላም የሚደረግን ጥሪ አሜን ብሎ መቀበል አለበት።
በአሶሣ ዩኒቨርሲቲ የማህበራዊ ሳይንስ መምህርና ዲን የሆኑት አበበ አኖም(ዶ/ር) ፥ ግጭቶችን በሰላማዊ መንገድ መፍታት የሚኖረው ፋይዳ በብዙ ነገሮች እንደሚገለጽ አንስተዋል፡፡
በተጨማሪም ችግሮችን በመነጋገር በመፍታት ለቀጣይ ትውልድ ሰላማዊ ሀገርን ማውረስ እንደሚገባም ነው ምሁራኑ ያስገነዘቡት።
በሲሳይ ዱላ
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/ ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!