የሀገር ውስጥ ዜና

በምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ርስቱ የተመራው ልዑክ በሀላባ ዞን የተከናወኑ የልማት ስራዎችን ጎበኘ

By Tibebu Kebede

June 03, 2020

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 26፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ)የደቡብ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ እርስቱ ይርዳ እና የደቡብ ብልጽግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት ሀላፊ አቶ ጥላሁን ከበደን ጨምሮ ሌሎች የክልሉ የስራ ሀላፊዎች በሀላባ ዞን የተከናወኑ የልማት ስራዎችን ጉበኙ።

በምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ የተመራው ልኡክ በሀላባ ዞን በአቶቲ ኡሎ ወረዳ በየዬ ቀበሌ የበቆሎ ሰብሎችን እና ሌሎች የበልግ አዝመራዎችን ጎብኝተዋል።