የሀገር ውስጥ ዜና

ዓመታዊውን የአረንጓዴ ዐሻራ ችግኝ ተከላ በመጪው ዓርብ በይፋ ይጀምራል- ጠ/ሚ ዐቢይ

By Tibebu Kebede

June 03, 2020

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 26፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) ዓመታዊውን የአረንጓዴ ዐሻራ ችግኝ ተከላ በመጪው ዓርብ በይፋ እንደሚጀምር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አስታወቁ።

ከኮቪድ 19 ወረርሽኝ ጋር እየተፋለምን ቢሆንም፤ 5 ቢሊየን ችግኞችን የመትከል ዕቅዳችንን እናሳካዋለን ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ።

እያንዳንዱ ቤተሰብ አካላዊ ርቀትን እንደ ጠበቀ ዐሻራውን ማሳረፍ የሚችልበትን መንገድ እንደሚመቻች ተጠቁሟል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ባለፈው ዓመት እያንዳንዳችን ሀገራዊ ጥሪውን ተቀብለን ያቀድነውን አሳክተናልም ነው ያሉት በፌስቡክ ገፃቸው።