የሀገር ውስጥ ዜና

ከዓድዋ ድል ጋር የተያያዙ ቅርሶች ለአዲስ አበባ ከተማ ተበረከተ

By ዮሐንስ ደርበው

February 07, 2024

አዲስ አበባ፣ ጥር 29፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ከተለያዩ ወረዳዎች የሰበሰባቸውን ከዓድዋ ድል ጋር የተያያዙ ቅርሶች ለአዲስ አበባ ከተማ አሥተዳደር አስረከበ፡፡

ቅርሶቹንም የክልሉ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ ምስኪያ አብደላ ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ጽ/ቤትና የካቢኔ ጉዳዮች ኃላፊ ጥላሁን ወርቁ አስረክበዋል፡፡

አሥተዳደሩ ያቀረበውን ጥሪ ተቀብሎ ከዓድዋ ድል ጋር የተያያዙ ቅርሶችን በማበርከቱም አቶ ወርቁ ለክልሉ ምስጋና ማቅረባቸውን የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ባህልና ቱሪዝም ቢሮ መረጃ አመላክቷል፡፡