የሀገር ውስጥ ዜና

ጠ/ሚ ዐቢይ (ዶ/ር) የትግራይ ክልል የመልሶ ግንባታና የሰላም ስምምነት አፈጻጸምን እየገመገሙ ነው

By Melaku Gedif

February 09, 2024

አዲስ አበባ፣ የካቲት 01፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ የነበሩትን ሥራዎች እና መሻሻሎች በጥልቀት መገምገም ጀምረዋል።

ይህ በፌደራል እና የክልል ኃላፊነት ባላቸው የሥራ ተዋንያን የሚደረገው ጠቃሚ ግምገማ በድኅረ ግጭት መልሶ ግንባታ እና በሰላም ስምምነት አፈጻጸም ላይ ያተኮረ መሆኑን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት መረጃ ያመላክታል፡፡