አዲስ አበባ፣ የካቲት 1፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በሶማሌ ክልል የዓለም የምግብ ፕሮግራም የሰብዓዊ እርዳታዎችን ለማሰራጨት በሚተገብረው አዲስ አሰራር ላይ ውይይት ተካሂዷል።
በመድረኩ የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳደር ሙስጠፌ መሃመድ፣ የዓለም የምግብ ፕሮግራም የሥራ ሃላፊዎች፣ የዞን አስተዳዳሪዎችና የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል።
ውይይቱ በዓለም የምግብ ፕሮግራም በኩል እርዳታ ለሚያስፈልጋቸው ወገኖች የምግብ እርዳታዎችን ለማሰራጨት በሚተገበረው አዲስ አሰራር ላይና ሌሎች አሰራሮችን ተግባራዊ ማድረግ በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ያረተኮረ ነው ተብሏል፡፡
በሌላ በኩል በዝናብ ወቅት የጎርፍ ሁኔታ እና የሕዝቡ አኗኗር ሁኔታ ላይ የተሰራ ጥናታዊ ጽሑፍ ቀርቦ ውይይት እንደተደረገበት የክልሉ መገናኛ ብዙሃን ዘግቧል፡፡