የሀገር ውስጥ ዜና

በደምቢ ዶሎ ከተማ ሕዝባዊ ውይይት ተካሄደ

By Feven Bishaw

February 10, 2024

አዲስ አበባ፣ የካቲት 2፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ)በኦሮሚያ ክልል በደምቢ ዶሎ ከተማ ሕዝባዊ ውይይት ተካሄደ፡፡

በውይይት መድረኩ የብልፅግና ስራ አስፈፃሚ አባልና በሚኒስትር ማዕረግ የብልፅግና ፓርቲ አደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ አቶ ሳዳት ነሻ ፣ የብልፅግና ፓርቲ ስራ አስፈፃሚ አባልና የአፋር ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኤሌማ አቡበከር ፣ የኦሮሚያ ፀጥታ እና አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ አራርሳ መርዳሳ እና ሌሎችም ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች ተሳትፈዋል።

በውይይት መድረኩ ከፍተኛ የመንግስት የሥራ ሃላፊዎች በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ከሕብረተሰቡ ጋር መክረዋል፡፡

መድረኩ” ህብረብሔራዊ ወንድማማችነት እና እህትማማችነት ለዘላቂ ሰላምና ሁለንተናዊ ብልፅግና “በሚለዉ መሪ ሃሳብ ነው የተካሄደው፡፡

በመራኦል ከድር