የሀገር ውስጥ ዜና

ጠ/ሚ ዐቢይ (ዶ/ር) ለቻይና ሕዝብና መንግስት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ

By Feven Bishaw

February 10, 2024

 

አዲስ አበባ፣ የካቲት 2፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ለቻይና ሕዝብ እና መንግሥት ለአዲሱ ዓመት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት÷አዲሱ ዓመት የብልጽግና እና የስኬት እንዲሆን መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል፡፡