አዲስ አበባ፣ ግንቦት 27፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በአዳማ ከተማ 77 ሺህ 575 ብር ሐሰተኛ የብር ኖት ከአሳታሚዎቹ ጋር በቁጥጥር ስር ማዋሉን የከተማዋ ፖሊስ መምሪያ ገለፀ ።
የአዳማ ከተማ ፖሊስ መምሪያ የህዝብ ግንኝነት ባለሙያ ረዳት ኢንስፔክተር ወርቅነሽ ገልሜቻ ዛሬ ለኢዜአ እንደገለጹት ሁለት ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር የዋሉት አንዱ ግለሰብ ሐሰተኛ ኖት ይዞ ወደ ገበያ በወጣበት ወቅት ከህብረተሰቡ በደረሰው ጥቆማ መሰረት ነው ።