የሀገር ውስጥ ዜና

ኮሚቴው ለጤና ተቋማት የሕክምና ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ

By ዮሐንስ ደርበው

February 13, 2024

አዲስ አበባ፣ የካቲት 5፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ዓለም አቀፍ የቀይ መስቀል ኮሚቴ በሰባት ከተሞች ለሚገኙ የጤና ተቋማት የሕክምና ቁሳቁስ እና የመድኃኒት ድጋፍ ማድረጉን አስታወቀ፡፡

በግጭት በተጎዱ አካባቢዎች የሚገኙ የጤና ተቋማት፣ የቆሰሉና የታመሙ ሰዎችን ለማከም የሕክምና ቁሳቁስ እና የመድኃኒት አቅርቦት እንደሚያስፈልግም ተመላክቷል፡፡

ይህን ተከትሎም ለወልዲያ፣ ላሊበላ፣ አላማጣ እና ቆቦ ሆስፒታሎች እንዲሁም ለሙጃ፣ ሮቢት እና ጀመዶ የጤና ማዕከሎች የሕክምና ቁሳቁስ እና የመድኃኒት ድጋፍ ማድረጉን ኮሚቴው ገልጿል፡፡

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/ ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!